የመለስ ዜናዊና የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት ንዋይ ገብረአብ መሞታቸው ተሰማ

የመለስ ዜናዊና የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት ንዋይ ገብረአብ መሞታቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

አቶ ንዋይ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ ሆኗል። ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት ያገለገሉት አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆንም ሠርተዋል።

በተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥም በአማካሪነት የሠሩት አቶ ንዋይ የአምባገነኑ ህወሓትና የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ መሆናቸውን ተከትሎ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ ህወሓት/ኢሕአዴግ በ’አሻንጉሊት’ ምንም ስልጣን ሳይኖራቸው እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር አስቀምጧቸው እንደነበር የሚነገርላቸው ኃይለማርያም ደሳለኝም ዋነኛ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን ዶክተር ዐቢይ ሥልጣኑን እስኪይዙ ድረስ በሓላፊነት ቆይተዋል::

ኢትዮጵያ በሁለቱም አገዛዝ በነብሩ አዎንታዊም ሆነ ለደረሱ የኢኮኖሚ ድቀት አቶ ንዋይ ከፍተኛ ድርሻ አንዳላቸው አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ

አቶ ንዋይ ከአዲስ አበባ እና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን  እንዳገኙ ከሕይወት ታሪካቸው መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY