በአረብ አብዮት ከሥልጣናቸው የወረዱት ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸው ተሰማ

በአረብ አብዮት ከሥልጣናቸው የወረዱት ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሆስኒ ሙባረክ ህይወታቸው ያላፈው ግብጽ ካይሮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ሳለ መሆኑ ተነግሯል።

ሆስኒ ሙባረክ እ.አ.አ. 2011 ላይ በግብጽ የአረብ አብዮት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአገሪቱ ጦር ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። የቀድሞው ፕሬዝደንት ግብጽን ለሦስት አስርት ዓመታት መምራታቸው ይታወቃል።

ሙባረክ ከሥልጣን በሕዝብ አመጽ ተገፍተው ከወረዱ በኋላ የአረብ አብዮት በተቀሰቀሰ ወቅት ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው እርምጃ በተባባሪነት ተጠያቂ ተደርገው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሦስት ዓመት በፊት የተመሰረቱባቸው ክሶች ውድቅ ተደርገው ነጻ ወጥተዋል።

የቀድሞ ፕሬዝደንቱን ህልፈተ ህይወትን ይፋ ያደረገው የግብጽ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ሙባረክ ከአንድ ወር በፊት የቀዶ ህክምና ማድረጋቸውን እና በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ መቆየታቸውን የቤተሰብ አባሎቻቸው ለግብጽ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል ።

LEAVE A REPLY