ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሀገር አቀፍና የክልል ፓርቲዎች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 በሚቆይ የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታቸውን አሟልተው እንዲመዘገቡ አሳሰበ፡፡
በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 162/2011 እና በዚሁ አዋጅ መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን ግዴታ ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር 03/2012 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ግዴታቸውን በመወጣት እንዲመዘገቡ የጊዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡
ቦርዱ እንዳሳወቀው እስከአሁን ድረስ ግዴታቸውን አሟልተው የተመዘገቡት ፓርቲዎች ቁጥራቸው አነስተኛ ነው ብሏል፡፡