በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ግንባታተጀመረ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ግንባታተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን ትራፊክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 835 ሚሊዮን ብር ወጪ እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስጀመሩ፡፡

ማዕከሉ የትራፊክ መረጃዎችን በማሰባሰብ የትራፊክ መብራቶች የቆይታ ጊዜን የትራፊክ ፍሰቱን መጠን የመቀያየርና ልዩ ልዩ የትራፊክ ፍሰት ማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወስዱ የማድረግ ተግባራትን ያከናውናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አከለ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ እንደተናገሩት ጣቢያው ባለአራት ወለል ሲሆን የወንጀልና አደጋ መከላከል ቢሮዎች የመረጃ ማደራጃና ሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያሰችል ሆኖ እንደሚደራጅ ተናግረዋል፡፡

የትራፊክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሕንፃው ባለ አራት ወለል ሲሆን 10 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ እንደሆነና ግንባታውም 18 ወራት እንደ ሚጠናቀቅና ለግንባታው 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በጀት መያዙን ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY