ሳዑዲ አረቢያ ለሃይማኖታዊ ጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎችን አገደች

ሳዑዲ አረቢያ ለሃይማኖታዊ ጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎችን አገደች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሳዑዲ አረቢያ ለሃይማኖታዊ ጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎችን አግዳለች።

በተያያዘም አንድ ጃፓናዊት ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ በመያዟ ምክንያትም ሐምሌ ወር ላይ ሊካሄድ የታሰበለት ኦሎምፒክ ሊሰረዝ ይችላል እየተባለ ነው።

የሳዑዲ መንግሥት የውጪ አገር ዜጎች ለሃይማኖታዊ ጉብኝት ወደ አገሩ እንዳይገቡ ማገዱን ይፋ አድርጓል። ይህ እገዳ ወደ መካ እና መዲና የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ጉብኝቶችንም ያካትታል።

ሐምሌ ወር ላይ የሚደረገው የሃጂ ጉዞ በዚህ እገዳ ምክንያት ሊሰረዝ እንደሚችል ግን አልታወቀም።

በተጨማሪም ሳዑዲ አረቢያ ኮሮናቫይረስ ከተከሰተባቸው አገራት የሚመጡ ሰዎች ወደ ድንበሬ ድርሽ እንዳይሉ አደርጋለሁ ብላለች። ሳዑዲ  ውስጥ እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልተገኘም።

LEAVE A REPLY