የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአ/አ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ከታከለ ኡማ ጋር አብረው ጎበኙ

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በአ/አ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ከታከለ ኡማ ጋር አብረው ጎበኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ከያኒያን በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ የቱሪስት መዳረሻ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ  ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ፕሮጀክቶቹን ለኪነጥበብ ባለሙያዎች ባስጎበኙበት ወቅት “ኪነ ጥበብ ማኅበረሰቡን እርስ በርሱ የማስተዋወቅ እና የማስተሳስር  አቅም አለው። በጠላትነት የሚፈላለጉ አካላትን በምትሃታዊ ሙዚቃ እጅ ለእጅ ተያይዘው ልባቸውን ለፍቅር ይከፍታሉ ” በማለት ተናግረዋል ።

ከኪነ ጥበብ ከያንያን ጋር በመሆን የከተማ አስተዳደሩ የሚሠራቸውን ሥራዎች በባለቤትነት መንፈስ በጋራ ለመሥራት እና ተሳትፎ ለማድረግ መነጋገራቸውን ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል ።

በጉብኝቱ የተሳተፉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር እና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ጠቁመው ፤ በኪነ ጥበብ ሥራዎቻቸው አስተዳደሩን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን  አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY