ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ጋር ተወያዮ

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ጋር ተወያዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር አባላት ጋር ዛሬ ተወያይተዋል:: የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር አባላቱ ከውይይቱ አስቀድሞ ሸገርን የማስዋብ እና እንጦጦ ላይ እየተካሄዱ ያሉ ሥራዎችን ጨምሮ፥ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጀመሩት የልማት ሥራዎች በኢንቨስትመንት አማካኝነት የመስፋፋት አቅም ያላቸው የትውልድ ሀብት መሆናቸውን ነው ለውይይቱ ተሳታፊዎች የተናገሩት።

አያይዘውም የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች ከተለያዩ ሰዎች ጋር ከሚያደርጉት ግንኙነት የተነሳ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እና የኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ዓይነተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ አድርጓል።

ለብልፅግና ጎዳናን ለመጥረግ የራሳችንን ገደቦች አልፈን መጓዝ ከቻልን የአገራችን ኢትዮጵያ ዕድገት አይቀሬ ነው ሲሉም ለማኅበራቱ አባላት የለውጡ ቡድን ፊት አውራሪ ማረጋገጫ ሰጥተዋል::

የታክሲ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ በተደረጉ የፖለቲካ ሽግግሮች ከፍተኛ አበርክቶ ያለው ሲሆን በተለይም ለንጉሱ ፍጻሜ የታክሲ ማህበረሰብ ያደረገው ሚና የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY