ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት አምስት ቀናት ግምታዊ ዋጋቸው 31 ሚሊየን 614 ሺህ 620 ብር የሚገመት የወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል።
የተያዙት ዕቃዎች አዳዲስና አሮጌ አልባሳትና ጫማዎች፣ የአይን መነጽሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምግቦች፣ የመዋቢያ ቁሳቁሶች፣ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዕቃዎች ናቸው።
ዕቃዎቹ በቦሌ አየር መንገድ፣ በባህር ዳር፣ ጅማ፣ ሁመራ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ፣ አዋሽ፣ ጋምቤላ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሂርና ወረዳ መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተያያዘ ዜና 161 ሺህ 513 የአሜሪካ ዶላር በድሬዳዋ፣ ሁመራ፣ በቶጎ ጫሌ እና በጅግጅጋ በኩል በሕገ ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር መዋላቸው ታውቋል።