ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 88 በመቶ መጠናቀቁ ተነገረ። ከሞጆ መቂ ከሚዘልቀው 56 ኪሎ ሜትር ውስጥ የ50 ኪሎ ሜትሩ ግንባታ መጠናቀቁን የግንባታ ሂደቱ በተጎበኘበት ወቅት ተገልጿል።
የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ 201 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን ከ13 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከአምስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል። የሞጆ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ በአራት ምዕራፍ ተከፍሎ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም ከሞጆ መቂ፣ ከመቂ ዝዋይ፣ ከዝዋይ አርሲ ነገሌና ከአርሲ ነገሌ ሃዋሳ የፍጥነት መንገዱ ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን ፤ በ2008 ዓ.ም የተጀመረው የመንገድ ፕሮጀክት በ2013 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል።
የመንገዱ ግንባታ የሃገሪቱን የወጪ ንግድ ከማሳለጥ ባለፈም ቀጠናዊና አህጉራዊ ትስስርን ለመፍጠር ግብ ላላት አፍሪካ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል እየተባለ ነው።