ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በዛሬው ዕለት መወያየታቸውን የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ በተደረገው ውይይት በተለያዩ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሠራዊቱ ዘንድ የሚከናወኑ ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ለውጦችን በተመለከተም ምዘና አድርገዋል።
በዚህ ጥልቅ ውይይትና ምክክር ላይ የመከላከያ ሠራዊት አመራር እና አባላት ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር አስደናቂ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አረጋግጠውላቸዋል።
በተጨማሪም አባላቱ ያላቸውን ሁሉ ለሀገራቸው ለመስጠት ቆራጥ እንደሆኑ አስታውሰው የሀገሪቱን ዘለቄታዊ ሠላም ለማስቀጠል የበለጠ እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የስብሰባው ጠቅላላ ሂደት እና አላማ በይፋ ባይገለጽም በህዳሴው ግድብ ዘረየ በሚነሱ አለመግባባቶች የግብፅ መሪ አልሲሲ በተደጋጋሚ ከጦር መሪዎቻቸው ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ተከትሎ ኢትዮጵያ አፀፋዊ ውይይት ለማድረግ የታለመ ነው ተብሏል።