የሟቾችን ዓመት የዘከሩት የቱሉ ፈራን ነዋሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን አገኘተወለ

የሟቾችን ዓመት የዘከሩት የቱሉ ፈራን ነዋሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ አድናቆትን አገኘተወለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተለምዶ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ተብል ከሚጠራው አካባቢ  ከዐስራ ሁለት ወራት በፊት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች የሙት ዓመት መታሰቢያ በአካባቢው ነዋሪዎች ተደረገላቸው

ባለፈው ዓመት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲበር የነበረና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን የስድስት ደቂቃ በረራ ካደረገ በኋላ ቢሾፍቱ አካባቢ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ሕይወት ማለፉ አይዘነጋም።

በአደጋው ሰሞን የሞቱት ሰዎች የሀዘን ወቅት 12 ቀን ሳይሞላው አልጋ ላይ አንተኛም በሚል ፍራሽ አንጥፈው፣ የነፍስ ይማር ጻዲቅ አዘጋጅተው እውነተኛ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያረጋገጡት የቢሾፍቱ ከተማ የቱሉ ፈራን  ነዋሪዎች ይህንን በተመሳሳይ ሁኔታ የአደጋውን ወቅት አንደኛ ዓመት በመታሰቢያ ዝግጅት አክብረውታል።

ዛሬ በተከናወነው የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ብሄር ጾታ ዘርና ቀለም የማይለዮት የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ሟችችን አስበዋል፤ ዘክረዋል:: የኦሮሞ ማኅበረሰብን ከሌላው የኅብረተሰብ ክፍል ለመነጠል ከፍተኛ ትግል የሚያካሂዱ ጥቂት ጽንፈኛ ፖለቲከኞች ከዚህን መሰሉ ንጹህ ኢትዮጵያዊነት ብዙ የሚማሩት ነገር እንደሚኖር ማወቅ አለባቸው የሚሉ አስተያየቶች ከተለያየ አቅጣጫ እየተሰሙ ነው።

የሟቾችን ዓመት የዘከሩት የቱሉ ፈራን  ነዋሪዎች የሰሩትን አኩሪ ገድል በአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ደረጃ ልዩ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ አድናቆትም ተችሯል።

LEAVE A REPLY