ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጉብኝት በማደረግ ለአባል ሀገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያን በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያላትን አቋም በማስረዳት ላይ መሆኑን ከደረሰን መረጃ መገንዘብ ችለናል።
በዚህም መሰረት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ኡጋንዳ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቷ በኡጋንዳ ቆይታቸው ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር ተገናኝተው በጉዳዮ ላይ በሥፋት መምከራቸው ታውቋል።
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የተመራ ከፍተኛ ቡድን ትናንት ኬንያ ናይሮቢ በመገኘት፤ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያላትን ግልጽ አቋም ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማስረዳቱ አይዘነጋም