ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ኮሮናን ለመከላከል በሚደረግ ድጋፍ ዙሪያ ከጃክ ማ ጋር ተወያዮ

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ኮሮናን ለመከላከል በሚደረግ ድጋፍ ዙሪያ ከጃክ ማ ጋር ተወያዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአፍሪካ ኖብል ኮሮና (COVID19) ሊያስከትል የሚችለውን የጤና ጉዳት ለመከላከል ቅድመ ዝግጁነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን መነጋገራቸውም ተሰምቷል።

ዛሬ  እሁድ ጠዋት ከጃክ ማ ጋር በአፍሪካ የCOVID19ን ስርጭት ለመግታት በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።

ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ኮሮናን መመርመሪያ ኪቶችን እና 100 ሺህ ማስኮችን ለማሰራጨት ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር በመምረጣቸው ጃክ ማንን  ዐቢይ አሕመድ አድንቀዋል።

የሚደረገው ድጋፍ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ለመንከባከብ የሚያስችሉ መመሪያዎችን አካትተው በቅርቡ የተዘጋጁ መጽሐፎችን እንደሚጨምርም ታውቋል።

የCOVID19 ስርጭትን ለመግታት ቁሳዊ ድጋፍን ከዕውቀት ጋር ማጣመር እንደሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አሰፍረዋል።

LEAVE A REPLY