አንባሳና ሸገር ባስ ለተሳፋሪዎች የእጅ ማጽጃ አልኮል ዛሬ ማቅረብ ጀመሩ

አንባሳና ሸገር ባስ ለተሳፋሪዎች የእጅ ማጽጃ አልኮል ዛሬ ማቅረብ ጀመሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአንበሳ እና ሸገር አውቶብስ አገልግሎት ድርጅቶች የተሳፋሪዎችን ንጽህና ለመጠበቅ ከዛሬ ጀምሮ የእጅ ማጽጃ አልኮል እንደሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተናገሩ ።

አሽከርካሪዎቹ የእጅ ጓንት የሚጠቀሙ ሲሆን ተሳፋሪዎችም ወደ አውቶቡሶች ሲገቡ ድርጅቱ የሚያቀርበውን የእጅ ማጽጃ አልኮል እጃቸው ላይ አድርገው እንዲገቡ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይልም በከተማዋ ጠንካራ ቁጥጥር እያካሄደ እንደሚገኝም ነው ከንቲባው የገለጹት።

የህዝብ አገልግሎት ሰጪዎችና በጎ ፈቃደኞችም አቅም የሌላቸውን እንዲሁም ውሀና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ማግኘት የማይችሉትን በተቻለን መንገድ እንዲደግፉም ጠይቀዋል።

በዛሬው ዕለት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲረዳ ለ15 ቀናት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዳይደረጉ ዛሬ በመንግሥትመወሰኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY