ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሊያካሂድ የነበረውን መደበኛ ስብሰባ የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ መንግሥት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት መሰረዙን ለአባላቱ አሳውቋል።
ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገጹ ለምክር ቤት አባላቱ የስብሰባውን መሰረዘ ባሳወቀበት ጽሑፍ ላይ ለስበሰባው መሰረዝ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባይገልጽም ከላይ የተቀመጠው እውነታ መሆኑ ተገምቷል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ ረፋድ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሰብሰባዎች እንዳይካሄዱ መወሰኑን ማሳወቃቸው ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት በአገሪቱ አስጊ ወደ ሆነ ደረጃ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የቀጥታ ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሣምንታት እንዲዘጉና ስብሰባዎችም እንዳይደረጉ መወሰኑን ተከትሎ በአዲስ አበባ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ከምሳ ሰዐት ጀምሮ የመማር ማስተማር ሂደቱን በማቋረጥ ተማሪዎችን አሰናብተዋል::