ኬንያ ያባረረቻቸው ሁለት ጣሊያኖችን ኢትዮጵያ ተቀበለች… || ታምሩ ገዳ

ኬንያ ያባረረቻቸው ሁለት ጣሊያኖችን ኢትዮጵያ ተቀበለች… || ታምሩ ገዳ

በትላንትናው እለት ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ኬንያ ያመሩ የጣሊያን ዜግነት ያላቸው ሁለት አገር ጎብኚዎች ከተሳፈሩት የኢትዮጵያ አውሮ ፕላን ሳይወጡ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተገደዋል።

ሲትዝን የተባለው የኬኒያ ቴሌቭዥን በድህረ ገጹ እንዳስፈረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነ አውሮፕላን ተሳፍረው ከሞምባሳው የሞይ አለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የደረሱት ፍራንሲስኮ እና ማርቤሎ የተባሉ ሁለቱ ጣሊያናዊያን አገር ጎብኝዎች “ይኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች የሚመስል ባህሪያት ታይቶባቸዋል” ተብልው ከተሳፈሩበት የኢትዮጵያ አውሮፕላን ሳይወርዱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የሞምባስ አካባቢ ኮሚሽነር የሆኑት ጅልበርት ኪቲዮ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።

እንደ ኮሚሽነር ጅልበርት ገለጻ ከሁለቱ ጣሊያኖች ጋር የነበሩ አርባ ሁለት ተጓዦች ተገቢው ምርመራ ከተደረገላቸው በሁዋላ ለቀጣዩ አስራ አራት ቀናት በማቆያ ስፍራ/ኳራንቲን/ ውስጥ እንዲቆይ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደረጉ በተባሉት ሁለቱ የጣሊያን ቱሪስቶች እጣ ፈንታ ዙሪያ እስከ አሁን ድረስ አግባብነት ያላቸው የመንግስት ባለስልጣናት የሰጡት አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ማብራሪያ የለም። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለሰራተኞቹ ሆነ ለተሳፋሪዎቹ ደህንነት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ ጠቅሶ አየር መንገዱ ወደ ባህሬይን የሚያደርገው በረራ ከዛሬ እሮብ ጀምሮ ለ ቀጣዩ አስራ አራት ቀናት መታገዱን አስታውቋል ።በረራው ያቆመው በአየር መንገዱ ፍላጎት ወይም በባህሬን መንግስት ውሳኔ ስለመሆኑ አልተብራራም።

በተያያዘ የኮሮና ቫይረስ ነክ ዜና ናይጄሪያ በጸረ ኮሮና ቫይረስ ላይ ያላትን ቁርጠኝነትን ለማጠንከር ስትል የወረርሺኙ መነሻ ከሆነችው ቻይናን ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ ታማሚዎች ከታዩባቸው አገራት ከጣሊያን፣ስፔን፣ኢራን፣አሜሪካ፣እንግሊዝ፣ ጃፓን፣ፈረንሳይ፣ሆላንድ፣ኖሮዌይ፣ስዊዘርላንድ፣፣ጀርመን፣ ደ/ኮሪያ ከመጪው አርብ መጋቢት /ማርች 20,2020 እኤአ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ግዛቷ ቢመጡ እንደማትቀበል የአገሪቱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማእከል ዛሬ አስታውቋል።

እንደ አሜሪካ፣የአውሮፓ ህብረት፣ ካናዳ፣ብሩንዲ፣ ቦትስዋና፣ አንጎላ ተመሳሳይነት ያለው ጥብቅ የጉዞ መመሪያ በተወሰኑ አገራት ላይ አውጥተዋል።ግብጽ ፣ሶማሊያ ጅቢቲ እና መሰል አገራትም በበኩላቸው ከካርጎ ጫኝ አውሮፕላኖች በቀር ሁሉም የመጓጓዣ አውሮፕላኖች ወደ ግዛታቸው እንዳይገቡ ቀጭን መመሪያ አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY