የፋናው ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ በኮሮና ተጠርጥሮ ራሱን ለይቶ ተቀመጠ

የፋናው ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ በኮሮና ተጠርጥሮ ራሱን ለይቶ ተቀመጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ በኮቪድ19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል መሆኑ ከጤና ሚኒስቴር ትላንት ማምሻውን ተገልጾለታል።

በዚህም መሠረት ከዛሬ መጋቢት 11/2012 ጠዋት ጀምሮ በመኖሪያ ቤቱ እራሱን ለይቶ ማቆየት መጀመሩ ታወቀ።

ጋዜጠኛ ማስረሻ ፍቅሬ ከአንድ ተራድኦ ድርጅት ጋር በነበረው የሥራ ግንኙነት ለበሽታው ሊጋጥ የሚችልበት ዕድል እንዳለ በመገመቱ ነው ራሱን እንዲለይ የተደረገው ሲሉ በፋና ውስጥ የሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል።

በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረው ግለሰቡ ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክት ያላሳየ እና  እስከ ትናትናው እለት ድረስ በስራ ገበታው ላይ የቆየ ሲሆን ጋዜጠኛውን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ሙከራ ያደረጉት ታማኝ ምንጮች እንዳልተሳካላቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY