ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ500 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት አፀደቀ።
ከዚህ ውስጥ 250 ሚሊየን ዶላሩ እርዳታ ሲሆን፥ ቀሪው ደግሞ በብድር የተሰጠ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል
ገንዘቡ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ዘላቂ ልማት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ይረዳል ተብሏል። ከዚህ ባለፈም በሃይልና በቴሌኮም ዘርፍ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን መደገፍና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ለመደገፍ ይውላልም ነው የተባለው።