ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች በራሳቸው ወጪ ለ14 ቀናት በሆቴል እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል።
ይህም የመንግሥት ውሳኔ ከትናንት በስቲያ ዕኩለ ሌሊት ጀምሮ በስካይላይት እና ግዮን ሆቴሎች ተፈጻሚ ሲሆን ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የሆቴሎች ቁጥር በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ 6 ሆቴሎች እንዲለዩ መደረጉን በጤና ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዚህም መሠረት፤ ጁፒተር፣ ኤሊያና፣ ማግኖሊያ፣ አዜማን፣ ቤስትዌስተርን እና ቦን ፕላዛ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኖች የሚቆዩባቸው ሆቴሎች ይሆናሉ ተብሏል።