በኢትዮጵያ በኮረና ቫይረስ ከተያዙት 12 ሰዎች 8ቱ አገግመዋል

በኢትዮጵያ በኮረና ቫይረስ ከተያዙት 12 ሰዎች 8ቱ አገግመዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱ ይታወቃል።

ከእነዚህም መካከል የ 8ቱ ሰዎች ጤና መሻሻል እየታየበት መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዶ/ር ተገኔ በቫይረሱ የተያዙት ሁለቱ ጃፓናውያን የጤና መሻሻል ካሳዩ በኋላ በእራሳቸው ጥያቄ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ሲሉተናግረዋል።

ከውጪ አገር መጥተው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ 85ዓመት እናት የጤና ሁኔታ አስጊ እንደነበረ አስታውሰው፤ የቅርብ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY