እጅግ ጠቃሚ የሐኪም ምክር ! || ሊያነቡት የሚገባ || ሚሚ ታደሰ

እጅግ ጠቃሚ የሐኪም ምክር ! || ሊያነቡት የሚገባ || ሚሚ ታደሰ

ዓለም ላይ በሰፊው የሃሳብ ፍጭት እየፈጠረ ስላለው የፀረ- ወባ መድሃኒት እና ስለ ኮሮና ቫይረስ ፈዋሽነት ጉዳይ የግል ዶክተሬጋ ደውዬ ያገኘሁት መረጃ ለሁላችንም ይጠቅመናልና እነሆ…

ጥያቄዬ እንዲህ ነበር:- “ኢትዮጵያ ላሉ ቤተሰቦቼ የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን እየጀመረ ስለሆነ ለቤተስቦቼ ፀረ- ወባ መድሃኒት ገዝቼ መላክ ፈልጌ ነበር እና ከመግዛቴ በፊት ሙያዊ ድጋፍ ፈልጌ ነበር” ብዬ ጥቄዬን አቀረብኩ።

የዶክተሬ ምላሽ፤ “መድሃኒት ገዝተሽ መላክ ፍፁም ስህተት ነው! ማድረግ የለብሽም። ከጅምሩ የኮሮና ቫይረስ የሚገለው በብዛት የጤና ችግር ያለባቸውን እና በእድሜ የገፉትን ነው። አንቺ መድሃኒቱን የምትልኪላቸው ሰዎች በእድሜ የገፉ እና አባሪ የጤና ችግር ያለባቸው ከሆኑ ከመድሃኒትነቱ ይልቅ ጉዳቱ የበለጠ ይሆናል። ምክንያቱም የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለምሳሌ ስኳር፤ የልብ ችግር፤ አስም ወይም ሌላ የፓቶሎጂ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሆኑ በሽተኞች ከሚጠቀሙት መድሃኒት ጋር ፀረ ወባ ኪኒኑ የሚፈጥረው የሁለቱ መድሃኒቶች ፍጭት (interaction) በበሽተኛውን አፋጥኖ ለሌላ ችግር እና ለፈጣን ሞትም ሊዳርገው ይችላል። በዚህ አይነት የጤና ችግር ላይ ያሉ ሰዎች መድሃኒቱ በጤና ባለሞያዎች መስጠቱ ብቻ ሳይሆን እንደበሽተኛው የኮሮና ቫይረስ ጥቃት መጠን ከአባሪ አንቲ ባዮቲክ ጋር ነው እየተሞከረ ያለው (ይሄ አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ለተጠቁ ሰዎች እየተሰጠ ያለ የሙከራ ህክምና ነው)። እዚህ ሙከራ ላይ የቫይረሱን መጠን መቀነስ ብቻ ሳይሆን ሳምባ ላይ የሚፈጠረውን ኢንፌክሽን የሚቀንስ ሌላ መድሃኒት መጨመር አለበት። ይኼ አንቲባዮቲክ ደግሞ ብይዘቱ ከሌሎች አንቲ ባዪቲኮች የሚለይ እና አሁን ላይ የባክቴሪያን ሳይሆን የቫይረስን ኢንፌክሽን የማከም አቅም ያለው እና በጤና ባለሞያዎች ብቻ የሚሰጥ ነው። ስለዚህ ከበድ ያለ ጥንቃቄ ስለሚያስፈልገው በጭራሽ በግል ለመጠቀም አይመከርም ሳይሆን አጥብቆ የተከለከለ ነው።”…

“የጤና ችግር ለሌለባቸው ፀረ ወባ መድሃኒት ገዝቶ ማስቀመጥ በቅርቡ በአለም ዙሪያ እያየን እንዳለነው የመፀዳጃ ቤት ሶፍት ገዝቶ የማስቀመጥ ያህል ነው። የኮሮና ቫይረስ በሽታ የአፍንጫ እርጥበትንም ይሁን ተቅማጥ እንደማያመጣ እየታወቀ ሰዉ ገበያ ውስጥ ሲፋጅበት ያየነው አይነት ክስተት ነው አሁንም ያፀረ ዋባ ማድሃኒት ላይ እያየን ያለነው። የኮሮና በሽታ ወጣቶችን ይዞ በራሱ የሚለቅ በሽታ ነው። በእርግጥ እንደግለሰቡ ትኩሳት ወይም ሳል ሊጠናበት፤ ከበድ ያለ ራስ ምታት፤ የአይን ብዥታ፤ የዕንቅልፍ ማጣት እና የመሳስሉት ሊሰማው በተጨማሪም ድካም እና ሆድ ህመም ሊፈጥር ይችላል። ሆኖም ግን በራሱ ጊዜ መዳን ለሚችል በሽታ አላስፈላጊ መድሃኒት መዋጥ ፍፁም አስፈላጊ አይደለም። እልቁኑ የራስ ምታትን እና ትኩሳት ለመቀነስ ፓራሴታሞል መጠቀም፤ ትኩስ ነገር አብዝቶ መውሰድ፤ መታፈንን ለማቀነስ የፈላ ውሃ ላይ ቪክስ አድርጎ እንፋሎት መታጠን ወይም ለኛ አገር (ለጋ ባህርዛፍ እንደማለት ነው) ልክ እንደ ኖርማል ከበድ ያለ የተስቦ ባሽታ እራስን በመንከባከብ፤ ቫይታሚን ሲ ነክ ማጠጦች አብዝቶ በመጠቀም ከአንድ ሳምንት እስከ ሁለት ሳምንት የሚወስደው የህመም ጊዜ እንዲያልፍ ማድረጉ የበላጠ ይመከራል እንጂ አሁን ባለው የእውሮፓ ተመክሮ በበሽታው የተያዙ ሁሉ ይዋጡ ተብሎ በፍፁም አይመከርም፤ አልፎም አልተወሰነም። የፀረ ወባ መድሃኒቱ መወሰድ ካለበት በህክምና ባለሙያ ምክር እና የመድሃኑቱ መጠን ተወስኖ እንጂ በግል የእራስን በሽታ በራስ በማከም ሂደት ውስጥ መሰጠት የለበትም” አለች።

ሁለተኛው ጥያቄዬ “ታዲያ ወጣቱ አውሮፓ ውስጥ ብዙዎችን እየገደለ ያለበት ምክንያት ምንድነው?” ብዬ ጠየቅኳት፥

ምላሿ፦ “አውሮፓ በብዛት እየሞቱ ያሉት በእድሜ የገፉ እና የጤና ችግር ያለባቸው፤ ከወጣቶች ደግሞ በተደጋጋሚ ለሳንባ ምች ወይም ለብሮንካይት የተጋለጡት፤ የአውሮፓ ማህበረሰብ ወጣቱ በለጋ እድሜው ከሲጋራ ጋር የተቆራኘ ሱስ ያላባቸው በተላይ የረጅም ጊዜ አጫሾች ነው ያጠቃው። በትክክል በሽታው የአደጋ ያህል በፍጥነት ሰለባ ያደረጋቸው ሰዎች ደግሞ በቨይረሱ ተይዘውም ብዙ ህመም ያልተሰማቸው እና ምንም አይነት ክትትል ሳያደርጉ ድንገት በሽታው በፍጥነት ተስፋፍቶ እኛም በትክክል አንድ የታማሚ መደብ ያላገኘንላቸው በቁጥር ትንሽ የሆኑትን ነው” ብላኛለች።

በመቀጠል የግል ዶክተሬ የቀድሞዋን ኢትዮጵያን ጠንቅቃ የምታውቃት በመሆኗ ካስተዋለችው ትልቅ ነጥብ አንዱ፡- “እናንተ አገር ከአውሮፓ እና ኤሲያ አገር ሲወዳደር የአዛውንቶች አገር ሳይሆን የወጣቶች አገር ነው። ይሄ ባሽታ ወጣቶችን ያማል እንጂ አይገልም! የእናንተ አገር አዛውንቶቻችሁ በጣም ቅርብ ጊዜ ነው የ 64 አመት የህይወት ዘመን ዕርከን ውስጥ የገቡት። አዛውንቶቻችሁ ድሮ ባደረጋችሁት ጦርናቶች አልቀዋል! አዲሱ ትውልድ ደግሞ ሊቋቋመው ይችላል” የሚል ተስፋ ሰጪ ሃሳብ ስታነሳ….. እኔ ደግሞ “ባሳለፍናቸው የመጨረሻው 25 አመታቶች ውስጥ አገራችን የተጠቃችበትን የኤች አይ ቪ ወረርሽኝ፤ እድሜን ያላማከለ የስኳር በሽተኛ ብዛት፤ የደም ብዛት እና ከአገራችን የአየር ብክለት ጋር ተያይዞ የአስም እና የመተንፈሻ አካል ችግር ያላባቸው ወገኖች ለችግሩ የተጋለጡ አይሆኑም ወይ?” የሚል ጥያቄ እንደመደምደመያ አቅርቤ ነበር፤ የዶክተሬ ምላሽ፦

“በኮሮና ጉዳይ የኤችአይቪ በሽታ ተጠቂዎች በህክምና ላይ ያሉትን ከማንኛውም ጤነኛ ሰው በተለየ መልኩ ለበሽታው ሊጋለጡ የሚችሉበት ምክንያት የለም! እስካሁንም አልታየም፤ የችግሩ ተጠቂዎች መደብ ውስጥም የሉም። አዋቂዎችም ይሁኑ ወጣቶች የስኳር በሽታ፤ የልብ፤ የአስም ወይም ሌላ የፓቶሎጂ በሽታ ኖሮባቸው የህክምና ክትትል የሚያደርጉ ሰዎች የመጀመሪያዎቹ መጠንቀቅ የሚገባቸው እና የሚያክሟቸው ዶክተሮቻቸው የሚሰጧቸውን የህክምና ፕሮቶኮል ብቻ መከተል ይኖርባቸዋል በግል የሚደረግ (auto medication) ግን ፍፁም የተከለከለ ነው። በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ካለባቸው የጤና ችግር ባሻገር የችግሩ ዋና ኢላማዎች ስለሆኑ ሙሉ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ለነሱ ነው ይሄ WHO ም ትኩረት የሚያመላክተው ይሄንን ነው” ብላለች።

በጥቅሉ የዶክተሬ ምክር ከፓራሴታሞል ውጭ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በራስ ትዕዛዝ መድሃኒት ገዝቶ ማስቀመጥም አለም የማፀዳጃ ቤት ሶፍት ላይ ከፈጠረችው ውዥምብር የተሻለ አይሆንም። በተቅራኒው የመተንፈሻ አካልን የሚነካ ህመም ያላባቸው ሰዎች ቫንቶላ ወይም አስም ሲያፍናቸው የሚጠቀሙት የመተንፈሻ አካልን መክፈቻ የመተንፈስ ችግርን በጊዜያዊነት ሊከፍት እና ዕራፍት ሊሰጥ ስለሚችል የአስም ታማሚዎች እንደ መጠበባበቂያ ቢኖራቸው ይመከራል። በተረፈ ግን በተስቦ በሽታ ወቅት የምንጠቀማቸው ማንኛውም አይነት ሳል ማስታገሻ፤ ትኩሳት መቀነሻ፤ ራስ ምታት ማስታገሻ ነገሮች አጥብቀው ይመከራሉ። የቫይረሱን ማጥፊያ ሳይሆን ሻይረሱ የሚያስከትለውን ህመምች ማስታገሻ መውሰድ ለታማሚዎች በከባድ ይመከራል። በተጨማሪም ያከለችው ትልቅ ተስፋ ስለ ፀረ-ወባም ይሁን፤ ሜዲቪር እና ሌሎችም ቀጥታ በሽተኞች ላይ እና በኪሊኒክ ሙከራ ላይ ያሉ መድሃኒቶች በቀጣዩ ሁለት ሳምንት እስከ አራት ሳምንት ውስጥ የኮሮና ህክምና ፕሮቶኮል ውስጥ የሚካተቱ እና ይፋ የሚሆኑ መድሃኒቶች ያለጥርጥር ስለሚኖሩ እስካዛ በጥንቃቄ መቆየት መልካም ነው ስትል በጥሞና አስረድታኛለች።

የእኔም የፅሁፌ መቋጫ የሚሆነው ከለምንም ንቀት እና ቀልድ አመታዊ ተስቦ ስንታመም የምንጠቀማቸው ማንኛውም ይህመም ማስታገሻ ከእራስን የማከሚያ ዘዴ ውስጥ መካተት አለባቸው። ለምሳሌ ጤናዳም ለሆድ ህመም፡ ፌጦ ለትኩሳት፤ የፈላ ወተት በነጭ ሽንኩርት እና በማር፤ ሎሚ በማር፤ የባህርዛፍ ቅጠል ሽታ የታፈነ አፍንጫን ለመክፈት፤ ዳማከሴ የራስ ምታትን ለመቀነስ፤ የውሃ ትነት የአተርን ድርቀት ለመከላከል፤ ሳልን ለማስታገስ ማንኛውም አይነት ትኩስ መጠጥ መጠቀም መልካም ነው ስል የግል ምክረ ሃሳቤን ጨምሬ ላብቃ።

በቀጣዩ የቤተሰን አባል የሆነ የሳንባ ባሽታ ስፔሻሊስት የሆነ ዘመዴን ጠይቄ የሚሰጠኝን ምክረ ሃሳብ አቀርባለሁ። እስከዛው እየታጠባችሁ፤ ባሃሳብ እና በመንፈስ መቀራረብ እንዳለ ሆኖ በርቀት እየተያያችሁ፤ እናንተም በቫይረሱ ሳትበከሉ፤ ከምንም በላይ ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖቻችንን ከእይታችሁ ሳታርቁ፤ ክትትል እና ጥንቃቄን በማድረግ ብትታደጓቸው እና እናንተም ወረርሽኙን በመግታት የምታተርፏት ሳምንት ሁሉ የቫይረሱ መድሃኒት የተገኘ ቀን ተጠቃሚ እንድትሆኑ ያደርጋል።
መልካም ምሽት ሚሚ ታደሰ ነኝ ከወርቃማው የቁም እስር ቤት (ፈረንሳይ)

LEAVE A REPLY