ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተመ ውስጥ በሽታውን ለመከላከል ለሕዝቡ መደረግ ያለባቸው አስፈላጊ ግብአቶች በተገቢው ሁኔታ እየተደረጉ እንዳልሆነ አስታወቁ።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በኢትዮጵያ አስጊ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዮ ከተሞች ተዘዋውረው እኔቅስቃሴውችን መመልከታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩት ፕሬዝዳንቷ ፤ “የሚጠጋን ቫይረስ የለም ሲሉ የነበሩ አገራት ያሉበትን እያየን አንዘናጋ” ካሉ በኋላ ፤ “መመሪያዎችን በመተግበር በኩል ገና ብዙ ይቀረናል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል ።
የበሽታው ምርመራ በስፋት ባለመደረጉ ያለው ትክለኛ ሁኔታ ስለማይታወቅ በአገር ደረጃ ተቀናጅቶ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ “ዛሬ በአአ ተዘዋውሬ ነበር እርምጃዎች መመርያዎችን በመተግበር ገና ብዙ ይቀረናል: የሚጠጋን ቫይረስ የለም ሲሉ የነበሩ ያሉበትን እያየን መዘናጋት የለብንም:: ምርመራ በብዛት ባለመደረጉ ትክለኛውን ሁኔታ አላየንምና” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል::