ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቀደም ሲል የነቀምቴ ከተማ የአስተዳደር እና የደህንነት ጽ/ቤት ሓላፊ ዛሬ ከሰዐት መገደላቸው ታወቀ።
ለዓመታት በሓላፊነት ያገለገሉት አቶ ተሾመ ገነቲ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ነው በጥይት ተመትተው መገደላቸው ጉዳዩን በቅርበት የተመለከቱ ሰዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከተማዋን በአስተዳድር እና ደህንነት ጽ/ቤት ሓላፊን ማን እንደገደላቸው የሚያረጋግጥ ይፋዊ መግለጫ የለም።
የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ደህንነት ቢሮ ምክትል ሓላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ሟቹ ግለሰብ በጥይት መመታታቸውን ከመስማታቸው ውጪ የተለየ መረጃ እንደሌላቸው ነው የገለጹት።
ከወር በፊት ከነበሩበት ሓላፊነት የተነሱትና በቀጣይ የሚመደቡትን አዲስ ሹመት በመጠባበቅ ላይ ሆነው የተገደሉትአቶ ተሾመ ፤ በ2007 እና በ2008 የነቀምቴ ጨለለቂ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ በመሆን ሠርተዋል። በተጨማሪም የከተማዋ የማህበራዊ ጽ/ቤት አመራር በመሆን ካገለገሉ በኋላ የነቀምቴ ከተማ የአስተዳደር እና የደህንነት ጽ/ቤት ሓላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።