ወደ ደቡብ ክልል ማንኛውም የትራንስፖርት ስምሪት እንዲቋረጥ ተወሰነ

ወደ ደቡብ ክልል ማንኛውም የትራንስፖርት ስምሪት እንዲቋረጥ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ሲባል ከዛሬ ዕኩለ ቀን ጀምሮ ወደ ደቡብ ክልል ማንኛውም የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት እንዲቋረጥ ተወሰነ።

በተያያዘ ዜናም በአሰላ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ መወሰኑም ተሰምቷል።

የደቡብ ክልል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ግብረ ኃይል እንዳለው አገር አቋራጭ ትራንስፖርትና ከክልል ወደ ክልል የሚደረግ የሕዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ መወሰኑን አመልክቷል።

የአሰላ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የባጃጆች እና ታክሲዎች እንቅስቃሴ እንዲቆም መወሰኑም ተነግሯል።

የደቡብ ክልልን የሚያቋርጡ ተሽከርካሪዎች ተሳፋሪን ሳያራግፉና ሳይጭኑ እንዲያልፉ የተፈቀደ ሲሆን በክልሉ ውስጥ በዞኖችና በወረዳዎች መካከል ያለው የትራንስፖርት ስምሪት ግን እንዲቋረጥ ተወስኗል።

በአሰላ ከተማ ከገጠር ወደ ከተማ እና ከከተማዋ ወደ ገጠር በታክሲዎች ሲሰጥ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ ነው የተገለፀው።

የደቡብ ክልል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ግብረ ኃይል ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመለሱ ተማሪዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች ግን በልዩ ሁኔታ የሚፈቀድላቸው እንደሚሆን ተገልጿል።

ግብረ ኃይሉ በተጨማሪም የከተማ ታክሲዎችና ባለሦስት ጎማ ተሽከርካሪዎች የሚያሳፍሩት ሰው መጠን ላይ ገደብ አስቀምጧል።

LEAVE A REPLY