የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከእነዚህም መካከል ክልል አቋራጭ የሆኑ የሕዝብ የትራንስፖርት አግልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጡ ተወስኗል።

በተጨማሪም በከተሞች ውስጥ የታክሲ፣ የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል የትራንስፖርት አግልግሎቶች በተመሳሳይ መልኩ ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጡ ተደርጓል።

የክልሉ መንግሥት በክልሉ ውስጥ ከአንድ ወረዳ ወደ ሌላ በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ተሽከርካሪዎች በግማሽ የመጫን አቅማቸው ብቻ እንዲሠሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከዚህ በተጫማሪም የትኛውንም ዓይነት ስብሰባ ማካሄድ እንደማይቻል ተነግሯል።

መጠጥ ቤቶች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት እና ሺሻ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል።

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙት ትልልቅ ከተሞች መግቢያ እና መውጫ ላይ የሙቀት ልኬት ማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ይጀመራልም ተብሏል።

ሕዝቡ በተቻለው መጠን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲገታና ወደ እምነት ቦታዎች ከመሄድ እራሱን እንዲቆጥብ ጥሪ ቀርቧል።

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን ለይቶ ማቆያ እንዲሆኑ ተወስኗል።

በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችም በተቻለ መጠን ከቤት ሆነው እንዲሰሩ የሚል ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን፤ የሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ሰዎችን በሕግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

LEAVE A REPLY