የአሜሪካው ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴዎድሮስ እድህኖም በበላይንት የሚመሩት፣ የአለም ጤና ተቋም ላይ የሰላ ትችት አቀረቡ፣ አገራቸው ለተቋሙ የምታፈሰው ገንዘብንም ለማቋረጥ ዝተዋል።
ማክሰኞ ጠዋት በወዳጆች መረብ ትዊተር ገጻቸው ላይ የጻፉት ፕ/ት ትራምፕ ” በአብዛኛው በአሜሪካ የሚደጎመው፣ የአለም ጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ አፍቃሪ ቻይና ነው። መልካም እጋጣሚ ሆኖ ድንበርሮችንን ለቻይና ክፍቱ ሲሉን ከመጀመሪያውኑ አልተቀበልናቸውም። ለመሆኑ እንደዚህ አይነት የተሳሳተ ሀሳብ ለምን ይሰጡናል?” ሱሉ ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ስር አለማቀፍ የጤና ጉዳዬችን የሚያተኩረው የጤና ተቋሙ (WHO,) ባለፈው የካቲት/ፌበርዋሪ 3,2020 እኤአ “በኮሮና ምክንያት የጉዞዎች እገዳ ማድረግ አያስፈልግም።” ብሎ ያወጣውን መግለጫን በማስረጃነት ተጠቅመውታል።
እንደ ዘ ሂል ድህረ ገጽ ዘገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም በዋና ኃላፊነት የሚመሩት የአለሙ ጤና ተቋም በአንዳንድ ወግ እጥባቂዎች አመለካከት “ድርጅቱ በቻይና ውስጥ የበሽታው ስር መስደድን በማድበስበስ፣ ሌሎች አገራት በቅድሚያ እንዳይዘጋጁ አዘናግቷቸዋል”፣ የሚል ወቀሳም ቀርቦበታል።
ከዚህ እና መሰል ትችቶ አኳያ በአሜሪካ የአሪዞና ግዛት የሪፖብሊካን ፖርቲ የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ሴንተር ማርትይ ምቲሳሉይ ባለፈው ሳምንት አፍቃሪ ትራምፕ በሆነው የፎክስ ኒውስ ቢዝነስ ፕሮግራም ላይ በሰጡት አስተያየት “እኛ እዚህ ሰዎች እየረገፉብን ቻይና የወረርሽኙ አስጊነትን መደበቋ፣ የአሜሪካ የመረጃ ክፍል የደረስበት በመሆኑ፣ የተነሳ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ስልጣናቸውን ሊለቁ ይገባል” በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል።
ሌላኛ ሪፖብሊካን እና የፍሎሪዳ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሪኤክ ስኮት እንዲሁ፣ “አለማቀፍ የጤና ተቋሙ የአለም ህዝብን በማዘናጋቱ፣ የአሜሪክ የአገር ውስጥ ደህንነት ክፍል በአለም ጤና ተቃም አሰራር ላይ ምርመራ ይካሄድ”፣ በማለት ጥሪ አቅርበዋል። እንደብዙዎች እምነት የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕም ሆኑ አስተዳደሯቸው ቢሆኑ የወረርሽኙ መንሰራፋትን በተመለከተ በመጀመሪያ ላይ ቀለል አድርገው መያዛቸው፣ በቂ የህክምና ቁሶችን አለማዘጋጀታቸው፣ የንግድ ተቋማት በአጭር ጊዜያት ይከፈታሉ ሱሉ በይፋ መናገራቸው በበርካታ አሜሪካኖች በተለየ በዲሞክራሲ ፓርቲ ተከታዮች ዘንድ በስፋት ተተችውበታል።