አዲስ አበቤ ከሰኞ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግለታል

አዲስ አበቤ ከሰኞ ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግለታል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ የቤት ለቤት  የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ ዋነኛ ትኩረት የተደረገባትና በርካታ ተጠቂዎች የተገኙባት አዲስ አበባ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።

በዚህም መሠረት የቫይረሱን የስርጭት መጠን ለመቆጣጠርና ቫይረሱ ወደ ሕዝቡ በምን ያህል ደረጃ ገብቶ እንደሆነ ለማረጋገጥ እንዲረዳ  የቤት ለቤት ምርመራ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን መስተዳድሩ አስታውቋል።

በቅድሚያ ለቫይረሱ ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ ወረዳዎች ምርመራው እንደሚጀምር የተናገሩት ከንቲባ ታከለ ኡማ በጠቅላላ በ117 ወረዳዎች የቤት ለቤት ምርመራው እንደሚካሄድ ይፋ አድርገዋል።

የፊታችን ሰኞ ለሚጀምረው የአዲስ አበቤዎች የቤት ለቤት ምርመራ በሥራ ላይ ያሉ፣ እንዲሁም የሕክምና ሙያ ያላቸውና በጡረታ ላይ የነበሩ ከ1200 በላይ  ሐኪሞች ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ታውቋል።

 

LEAVE A REPLY