ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጅቡቲ በኩል ኢትዮጵያ ልታስገባው የነበረ የምግብ ሸቀጦች ላይ የተጣለ ገደብ አለመኖሩን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
በትናንትናው ዕለት አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ቤት ልታስገባው የነበረ የምግብ ሸቀጥ ወደብ ላይ መታገቱንና ግማሹን የጅቡቲ መንግሥት ለአገሩ ዜጎች እንዲከፋፈል አድርጓል ሲሉ ያሰረጩት ዘገባ ፈጽሞ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው በማለት በኤምባሲው ድህረ ገፅ በኩል ያሳወቀው የኢትዮጵያ መንግስት ሚዲያዎቹ መረጃውን በማረም እንዲያቀርቡም አሳስቧል።
“የተከሰተው ችግር መነሻ ከጉምሩክ አሠራር ጋር የተያያዘ ነው ይህን ተከትሎም ኤምባሲው ችግሩን በፍጥነት ለመፍታት በጅቡቲ ከሚመለከታቸው የሥራ ሓላፊዎች ጋር በመነጋገር ላይ እንገኛለን ብሏል።
በጉዳዮም ላይ የኢትዮጵያና የጅቡቲ መንግሥት እየመከሩበት ነው” ያለው በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ የንግድ ቀጠና ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል ተገዝቶ የተከማቸ ምንም ዓይነት የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ የለም ሲል ማረጋገጫ ሰጥቷል።