ወደ ትግራይ የሚገቡ ማናቸውንም ተጓዦች ለይቶ ማቆያ ማስገባት ጀመረ

ወደ ትግራይ የሚገቡ ማናቸውንም ተጓዦች ለይቶ ማቆያ ማስገባት ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ህወሓት መራሹ የትግራይ ክልል መንግሥት ከየተኛውም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ ሰዎችን ወደ ለይቶ ማቆያ ማስገባት ጀመረ።

ከማዕከላዊ መንግሥት ባፈነገጠው ህወሓት የምትተዳደረው ትግራይ ከትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ በአሉላ አውሮፕላን ማረፊያ የሚገቡ መንገደኞች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉ ታውቋል።

የዶ/ር ደብረፂዮን መንግሥት ትናንት ወደ ለይቶ ማቆያ የወሰዳቸው ሰዎች 47 ሲሆኑ ተጓዦቹ በማቆያው ለ14 ቀናት በሚቀመጡበት ወቅት ወጪያቸውን ሙሉ በሙሉ ራሳቸው እንደሚሸፍኑ ገልጿል።

የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ በአውሮፕላን ወደ ትግራይ የሚሄዱ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ሳይገቡ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ  ባካሄደው አስቸኳይ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ስብሰባ ይህንን የለይቶ ማቆያ ውሳኔ ከማፅደቅ ባሻገር ቀደም ሲል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለቀጣይ ሦስት ወራት ተፈጻሚ እንዲሆኑ ወስኗል።

LEAVE A REPLY