ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ዛሬ ተረጋገጠ

ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ዛሬ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በየቀኑ አዳዲስ ቁጥሮችን እያስመዘገበ ያለው የኮሮና ቫይረሰ በአዲስ አበባ እየጨመረ መጥቷል።  በዛሬው ዕለትም ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ መያዛቸው ይፋ ተደርጓል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ እንደገለፁት ከሆነ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ447 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ስምንት ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ነው የገለፁት።

አሁን ላይ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና ከውጭ ከመጡ ሰዎች ጋር ንክኪ የሌላቸው አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው አሳሰቢ ሆኗል።  የቫይረሱን ስርጭት በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚከበረውን የፋሲካ በዐልን ተንተርሶ በሚደረገው ግብይት በሚከሰተው መጨናነቅ ብዙኃኑ ኅብረተሰብ ለበሽታው ተጋላጭ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ከወዲሁ እየተሰማ ነው።

በኢትዮጵያ በ4557 ሰዎች የኮቪድ 19 ምርመራ ተደርጓል። ባለፉት በ24 ሰዓታት ውስጥ ደግሞ  ለ447 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በጠቅላላ 82 ሰዎች የቫይረሱ ተጠቂዎች መሆናቸው ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY