በኦሮሚያ ሰዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ዳግም የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

በኦሮሚያ ሰዎችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች ላይ ዳግም የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል ሰዎችን እንዲያጓጉዙ የተፈቀደላቸው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በሚያስከፍሉት ተመን ላይ ዳግም ማሻሻያ ተደረገ።

ቀደም ሲል ከአንዱ የክልል ወረዳ ወደ ሌላ ወረዳ፣ ከዞን ወደ ዞን የሚደረጉ፤ እንዲሁም ከአጎራባች ከተሞች  ወደ አዲስ አበባ ሰዎችን የሚያጓጉዙ መኪኖች ከመጫን አቅማቸው በግማሽ እንዲቀንሱ ተደርገው ሢሠሩ ቆይተዋል።  በዚህ መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ተሳፋሪዎችም ተጨማሪ የአንድ ሰው ክፍያ (እጥፍ ዋጋ) እንዲፈጽሙ ሢደረግ ሰንብቷል።

በተጠቀሰው የተጋነነ የጉዞ ክፍያ ታሪፍ ምክንያት የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል አባላት ተጎጂ በመሆናቸው ዳግመኛ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል።

የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሕመድ አባ ጊሳ  ሰሞኑን ከሕዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ተሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በተወሰነው መሠረት ከመጫን አቅማቸው በግማሽ መጠን ቀንሰው መሥራታቸውን እንዲቀጥሉ፣ ተሳፋሪዎች ደግሞ የራሳቸውን ሂሳብና የሌላ ተሳፋሪን ግማሽ ክፍያ ብቻ እንዲፈጽም ከስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY