የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክሶች ብቻ የሚያይ ችሎት ተዘጋጀ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክሶች ብቻ የሚያይ ችሎት ተዘጋጀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በሚመለከት የሚቀርቡ ክሶችን የሚያዮ ችሎቶች እንደተዘጋጀ ጠቅላይ ፍ/ቤት ገለጸ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተዘጉት የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በደንቦችን በሚተላለፉ ክሶችን የሚመለከቱ ችሎቶች እንደተዘጋጁ አስታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያወጣውን ዝርዝር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንብን ተከትሎ፤ ደንቡን ተላልፈዋል በሚል በዐቃቤ ሕግም ይሁን በሌላ ፀጥታ አካል የሚቀርቡ ክሶችን ለማየት በየችሎቶቹ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከመጋቢት11 ጀምሮ ፍርድ ቤቶች ዝግ ሆነው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

LEAVE A REPLY