ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የኮሮና ታማሚዎችን ጠየቁ ፣ ለሕክምና ባለሙያዎች ስጦታ አበረከቱ ጠቅላይ ሚኒስትር...

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የኮሮና ታማሚዎችን ጠየቁ ፣ ለሕክምና ባለሙያዎች ስጦታ አበረከቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ያሉበት የሕክምና መስጫ ቦታ ድረስ በመሄድ ጠይቀዋል:: የብልፅግና ፓርቲ ሊቀመንበር በየካ ሆስፒታል የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን በጎበኙበት ወቅት ሕመምተኞቹ አገግመው ይወጡ ዘንድ ያላቸውን መልካም ምኞትም ገልጸዋል:: ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተካተቱበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥየቃ ፕሮግራም የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የተደረገ መሆኑን የተለያዮ የዜና አውታሮች በመዘገብ ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለም ዐቀፍ ወረርሽኙ የተጠቁ ዜጎች በፍጥነት እንዲያገግሙና ወደ ነበሩበት የሕይወት ዘዬአቸው እንዲመለሱ ከመመኘታቸው ባሻገር ፤ በሄዱበት የካ ኮተቤ ሕክምና መስጫ እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስጦታዎችን በማበርከት ወገንን በሙያቸው ለመታደግ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦም አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ  የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ያሉበት የሕክምና መስጫ ቦታ ድረስ በመሄድ ጠይቀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ሊቀመንበር በየካ ሆስፒታል የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን በጎበኙበት ወቅት ሕመምተኞቹ አገግመው ይወጡ ዘንድ ያላቸውን መልካም ምኞትም ገልጸዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ኢንጂነር ታከለ ኡማ  የተካተቱበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥየቃ ፕሮግራም የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የተደረገ መሆኑን የተለያዮ የዜና አውታሮች በመዘገብ ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  በዓለም ዐቀፍ ወረርሽኙ የተጠቁ ዜጎች በፍጥነት እንዲያገግሙና ወደ ነበሩበት የሕይወት ዘዬአቸው እንዲመለሱ ከመመኘታቸው ባሻገር፤ በሄዱበት የካ ኮተቤ  ሕክምና መስጫ እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስጦታዎችን  በማበርከት ወገንን በሙያቸው ለመታደግ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦም አድንቀዋል።

LEAVE A REPLY