የዶሮና እና እንቁላል ምርቶችን ሽያጭ በሸማች ማኅበር በኩል ሊደረግ...

የዶሮና እና እንቁላል ምርቶችን ሽያጭ በሸማች ማኅበር በኩል ሊደረግ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዶሮና እና  እንቁላል ምርቶችን  በሸማች ማኅበር  በኩል ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ ድርድር እየተደረገ ነው

ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚከበረው የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል በዶሮ አርቢዎች፣ አቀናባሪዎች እና ላኪዎች ማኅበር ክምችት የሚገኝና ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት፣ በሸማች ማኅበራት በኩል ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ ድርድር እየተካሄደ መሄዱ ተሰማ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሆቴሎችና ሬስቶራንቶች ሥራ መቀዝቀዙ (አንዳንዶቹም መዘጋጀታቸው) እንዲሁም በዐቢይ ፆም ወቅት የነበረው የፍላጎት መቀነስ  ምክንያት ከፍተኛ መጠን ያለው የዶሮና እንቁላል ክምችት እንዲፈጠር ማድረጉ እየተነገረ ነው።

ጉዳዮ የሚመለከተው የኢትዮጵያ የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይለስላሴ ወረስ ለእንደገለፁት ማኅበሩ ከ124 ሺህ በላይ  ዶሮዎች እንዳሉት ፣ ከ312 ሺህ ቶን የሚልቅ የዶሮ ስጋ እና ከአራት ሚሊየን በላይ እንቁላሎች እንደያዘ አረጋግጠዋል።

ምርቶቹ ኅብረተሰቡ ለፋሲካ በዓል በሸማች ማህበራት በኩል እንዲገዛቸው ድርድር እየተካሄደ ነው ያሉት ሓላፊው ፤

ድርድሩን እያካሄዱ ያሉት የዶሮ አርቢዎች፣ አቀናባሪዎችና ላኪዎች ማኅበር ፣ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኩል ከሸማች ማህበራት ጋር እንደሆነም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት  በበኩሉ ሁለቱ ወገኖች ተቀራርበው እንዲነጋገሩ ሁኔታዎችን አመቻችቷል::

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የቁም እንስሳት ስጋ  ላይ ያለውንፍላጎት እንዳላቀዘቀዘውና ተፅዕኖ እንዳላሳደረ የጠቆሙት  ዋና ዳይሬክተሩ ከሰሞኑ እንኳን የተባበሩት ዐረብ ኢሚሬትሷ ዱባይ በአንድ ጊዜ አንድ መቶ ቶን የቁም እንስሳት ስጋ ከኢትዮጵያ መግዛቷን ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY