የኩላሊት ታማሚዎች ለኮሮና ቫይረስ በሰፊው ተጋላጭ ናቸው ተባለ

የኩላሊት ታማሚዎች ለኮሮና ቫይረስ በሰፊው ተጋላጭ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኩላሊታቸው ሙሉ ለሙሉ ሥራ አቁሞ፣ በኩላሊት እጥበት ወይንም ዲያሊስስ እገዛ እየኖሩ ያሉ ዜጎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከመከሰቱ አስቀድሞ በርካታ ዜጎችን ሲቀጥፍ የቆየው የኩላሊት በሽታ ለጊዜው ቢሆንም በገዳዮ ቫይረስ ስጋትና ሰፊ የዜና ሽፋን የተረሳ ቢመስልም አሁንም ሁለቱ ኩላሊታቸው ሥራ አቁሞ በህመም የሚሰቃዮ በርካታ ሰዎች በየሆስፒታሉና በየቤቱ አሉ።

ኮሮና ኩላሊት ታማሚዎች በብዙ መልኩ ባላንጣ ሆኗል ማለት ይቻላል:: በተለያዮ የመዲናዋ አካባቢዎች የንቅለ ተከላና የዲያሊስስ ወጪ ለመሸፈን በመኪና ላይ በሚየደርጉት የልመና ቅስቀሳ በእጅጉ ቀንሷል:: ዓለም ላይ ብዙኃንን የቀጠፈው ኮሮና ዜጎችን ከእሱ ውጪ አስገድዷቸዋል እየተባለ ነው:: ሰዎች በብዛት በየቤታቸው መከተታቸው በራሱ በሰዎች እርዳታ ሕይወታቸውን ለማድረግ ተስፋ ያደረጉ ታማሚውችን ሕልማቸውን አደብዝዞባቸዋል::

የሕክምና ባለሙያዎች በበኩላቸው ኮቪድ 19 ቫይረስ ተጓዳኝ በሽታ ያለባውን ሰዎች የማጥቃት ባህሪይ ያላቸው መሆኑን ከመግለፅ ባሻገር በተለይ የዲያሊስስ ሕክምና የሚያደርጉ የኩላሊት ታማሚዎች የበለጠ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚህኑበት ዕድል ሠፊ እንደሆነ መጠቆማቸው የታማሚዎቹ ዋነኛ ስጋት መሆኑን መረዳት ተችሏል::

በመሆኑም ሕሙማኑ እንደ በሼታው የዕድገት መጠን በሳምንት ውስጥ ለተለያዮ ቀናት የዲያሊስስ ሕክምና ለማድረግ ወደ ሕክምና ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ በማሰብ  ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ተመቻችትላቸዋል::

ለ800 ያህል የኩላሊት እጥበት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ይህንን በጎ ተግባር እየፈጸሚ ያሉት ለጊዜው ሁለት የታክሲ ማህበራት ይሁኑ እንጂ በቀጣይ ሌሎች በመዲናዋ የሚገኙ የታክሲ ማኅበራትና መሰል ተቋማት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ጉዳዮ ከሚመለከተው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡

LEAVE A REPLY