ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት ከጥቂት ሣምንታት በፊት ያወጣውን የኮሮና ቫይረስ አስገዳጅ ሕግን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በራሳቸው ወጪ ወደ ለይቶ ማቅያ የገቡ ሰዎች በአሠራር ረገድ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳላቸው ገለፁ::
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከውጪ የሚመጡሰዎች በአስገዳጅ ሁኔታ በለይቶ ማቆያ ለ14 ቀን እንዲቆዩ መመሪያ ተላልፎ ሥራው መሠራት ከጀመረ ቢሰነባብትም በለይቶ ማቆያው የሚገኙ ሰዎች ከተባለው 14 ቀን ውጪ ለ21 ቀናት እንዲቆዮ እየተገደዱ መሆናቸውን ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል::
ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ዜጎች መንግሥት ያወጣውን መመሪያ በማክበር በራሳቸው ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያዎች ቢገቡም ወደ ሀገር ቤት ሲመጡ አስቀድመው ከያዙት ፕሮግራም ውጪ ለተጨማሪ ቀናት እንዲቆዮ መደረጋቸው በኢኮኖሚ ና በወጠኗቸው ዕቅዶች ላይ እንቅፋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል::
ከምንም በላይ ለ14 ቀን ገብተው እስከ 21 ቀን ድረስ እንዲቆዮ መደረጋቸው ለሳይኮሎጂ ስጋት እንደዳረጋቸው የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በተለይም ተዛማጅ በሽታ ያለባቸው በለይቶ መቆያ ያሉ ተመላሾች የሕክምና ባለሙያዎች ዞር ብለው እንደማያይዋቸውና ምንም ዓይነት ክትትል እንደማያገኙ ቅሬታቸውን ገልጸዋል::