“ሰይጣን ቤት” የህወሓት ማሰቂያ  እንደነበር ተሰማ፤  መሳሪያዎች ተደብቀው ተገኙ

“ሰይጣን ቤት” የህወሓት ማሰቂያ  እንደነበር ተሰማ፤  መሳሪያዎች ተደብቀው ተገኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት በሆነው ሰይጣን ቤት ዛሬ ሊፈርስ እንደነበር በተሰማው መረጃ መሰረት በመሄድ ድርጊቱን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደስፍራው  አምርተዋል።

ሰይጣን ቤት እንደማይፈርስና እንዲያውም እድሳት እንደሚደረግለት ነው የተገለጸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነበር በህንጻው አካባቢ የተከማቸ ፍርስራሽ ውስጥ በርካታ የጦር መሣሪያዎች ተደብቀው የተገኙት።

በተለያዮ ምሁራን  ብዙ የተፃፈለት እና የታሪካችን አካል የሆነው “ሰይጣን ቤት” ዛሬ በውስጡ የተለያዮ የጦር መሣሪያዎች ተደብቀው ተገኝተውበታል።

ለረዥም ጊዜ ዙሪያውን ፈርሶ በቆየው በዚህ ታሪካዊ ስፍራ ውስጥ የጦር መሳሪያ ምን ሊያደርግ ተቀመጠ? የሚለው ጉዳይ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው::

ሲኒማ ቤት ተብሎ በሩ ላይ ቢለጠፍም ተቋሙ ፊልም ማሳየት ካቆመ  በርከት ያሉ ዓመታት ቢቆጠሩም አዳራሹን ሕወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ የሰብአዊ ገፈፋ ይፈፀመበትና በፖለቲካ አመለካከታቸው ልዩነት ብቻ ሰዎች ይሰቃዩበት እንደነበር ነው የተሰማው።

ተደብቀው የተገኙት መሳሪያዎችም ከሰይጣን ቤት ጋር ድንበር የሚጋራውን ሜጋ ኪነ ጥበባት ማዕከልን ሲያስተዳድር የቆየው ህወሓት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ አምባገነኑ ሥርዓት ለጥፋት ተልዕኮው ደብቆ አስቀምጦት የነበረ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው::

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰምኑን እየወሰደ ያለውን ልማትን መሠረት ያደረገ የማፍረስ ዕቅድ ውስጥ ገብቶ የነበረው የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት (ሠይጣን ቤት) ታሪካዊ ቅርስ ነው ቤቱ አይፈርስም  በሚል የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።  ስለ ተገኘው የጦር መሣሪያ ግን በፖሊስ በኩል የተሰጠ ይፋዊ ማብራሪያ የለም።

LEAVE A REPLY