ሚያዝያ 2012
በደርግ ዘመን ሰው አውሬ ሆኖ ‹‹ዛሬኮ አንድም አልገደልኩም!›› በሚባልበት ክፉ ዘመን በጉለሌ ኪዳነ ምሕረት (ይመስለኛል) የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ንግግር ተጋብዤ ምነው ግፍን በየመንገዱ እያየን ሁላችንም ዝም አልን? በማለት አሳዝኜ ነበር፤ በእንግሊዝኛ፤ ከዚያም እግግዚአብሔርን ተቆጥቼው ነበር! ፡—
አረ ስማ እግዚአብሔር!
ተቸገረ ፍጡር፤
እስከመቼ ድረስ ዝም ብለህ ታያለህ?
አይሰለችህም ወይ አቤት! አቤት! ሲሉህ?
ቸግሮህ ይሆን ወይ ብልሃቱ ጠፍቶብህ?
ባንተው እጅ ሥራ በገዛ ትንፋሽህ!
….
የኢጣልያ ፋሺስት ግፍ፣ የጃንሆይ ማባበል፣ የደርግ ጭካኔ፣ የወያኔ እኩይነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ምንም አላስተማረውም፤ ዛሬ ኮሮና አስተምሮት እንደሆነ እናያለን፤ እኔ ግን አይመስለኝም፤ እንዲሁ ሲናደድ እየደቆሰ ያስለቅሰናል እንጂ! እኛም አናርፍ እሱም አይለቀንም! እርስበርሳችን ማፋጀቱ የማያርመን ሲሆንበት ይቺን ለዓይን የማትበቃ ገዳይ ላከብን!
የየሃይማኖቱን ካህናት እንደኮሮና አፋቸውን የፈታላቸውና ነጻነት የሚባል ነገር መኖሩን ያሳወቃቸው ጊዜ የለም!