ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጡት 116 ሰዎች መካከል አምስት ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል ተባለ::
በዚህም መሠረት ከበሽታቸው ያገገሙ ሰዎች ቁጥራቸው 21 ደርሷል። ከገዳዮ ቫይረስ ያገገሙት አምስቱ ሰዎች በለይቶ ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ሆነው ሕክምናቸውን ሲከታተሉ (አራቱ ከአዲስ አበባ ፣ አንዱ ከድሬዳዋ) የነበሩ መሆናቸውን ከመግለጫው ሰምተናል።
በሀገሪቱ እስከዛሬ ድረስ ሲካሄድ ከነበረው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጠን በእጅጉ በጨመረ መልኩ ፤ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ከአንድ ሺኅ በሚበልጡ ሰዎች ላይ ምርመራ በማድረግ ፣ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።
ከሌሎቹ ቀናት በተለየ የቫይረሱ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች 1023 ናቸው ያለው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርበሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ሁለት ብቻ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
በቫይረሱ ከተያዙት ሁለት ሰዎች መካከል አንደኛው በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ ነዋሪና የውጪ ጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሲሆን፤ በቫይረሱ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ እየተጣራ መሆኑን ገልጿል። ሁለተኛው በሽታው የተገኘባቸው ግለሰብ ግን ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።