በከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዐት ገደብ ተነሳ

በከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዐት ገደብ ተነሳ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲሰ አበባ በከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዐት ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ መነሳቱ ታወቀ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት  ቢሮ በከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረው የሰዐት ገደብ ከወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ላልተወሰነ ጊዜ መነሣቱንና ወደ ቀድሞ አሠራሩ እንዲመለስ መደረጉን ዛሬ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በተቋሙ ቀደም ሲል ወጥቶ የነበረው ገደብ የተነሣው ፤ ከመጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም  ጀምሮ ኢትዮጵያ መግባቱ የተረጋገጠው የኮሮና ቫይረስ ፤ በሸቀጣ ሸቀጥ እና ሌሎች ምርቶች ላይ እጥረት ወይም ያልተገባ የዋጋ ጭማሪእንዳይከሰት ፣ እንዲሁም የሸቀጣ ሸቀጥ ስርጭት እንዲመቻች ታሳቢ በማድረግ  እንደሆነ መሆኑን የቢሮው የኮሚኒኬሽን ሓላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል።

ይህን መመሪያ ተከትሎ ከዛሬ ሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ከባድ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ለ24 ሰዐት ያለ ምንም ገደብ መንቀሳቀስ ይችላሉ መባሉን አረጋግጠናል።

LEAVE A REPLY