ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ሲባል በድሬደዋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ ሊገድብ እንደሚችል የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።
የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሓላፊ ወይዘሮ ለምለምበዛብህ ኮቪድ 19 ድሬዳዋ ላይ ካሳደረው ስጋት አንፃር የሥርጭት ሁኔታው ታይቶ እንቅስቃሴ ሊገደብ ስለሚችል፣ የከተማው ነዋሪ ዝግጁ እንዲሆን መልዕክት እንዳስተላለፉ ታውቋል።
እስካሁን ቫይረሱ በሰውነታቸው የተገኘባቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ የነበሩ መሆናቸውን ያመላከቱት ከንቲባዋ ፤ “ሆኖምበከተማው ወይም ከገጠሩ ከኅብረተሰብ ናሙና ተወስዶ ተመሳሳይ ምልክት ከተገኘ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴን ከማቆም ወደኋላ አንልም” ሲሉ ነው የተናገሩት።
የመተንፈሻ አካል ህመም ያለባቸው ሰዎች ናሙና አሁን ላይ እየተወሰደ መሆኑን እና አንድም ሆነ ሁለት ሰው በቫይረሱ ተጠቅቶ ከተገኘ ከተማዋን ወደ መዝጋት እንሄዳለን ነው ያሉት ከንቲባዋ::
“የከተማው እንቅስቃሴ ቢዘጋ፣ የችግሩ ስፋት እስከምን እንደሚዘልቅ መገመት አንችልም፣ በጣም ተጋላጭ በመሆናችን አሁንም ባለሀብቱ በዓይነትና በገንዘብ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” በማለት ስጋታቸውን የገለፁት ከንቲባ ለምለም ቀደም ሲል ባለሀብቶች ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል