ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ ተጨማሪ 5 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር አስታወቀ።
ለ1 ሺህ 19 ሰዎች ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የገለፁት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፤ በተደረገው ምርመራ ተጨማሪ 5 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 122 መድረሱን ጠቁመዋል።
ዛሬ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ከተባሉት ሰዎች ውስጥ አንዷ የ75 ዓመት እድሜ ያላቸው ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ሴት ከመሆናቸው ባሻገር፣ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳላቸውም እየተጣራ ይገኛል ተብሏል።
አራቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ39፣ የ49፣ የ59 እና የ28 ዓመት እድሜ ያላቸው ቻይናውያን ሲሆኑ፥ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው መሆኑን ከሚኒስትሯ መግለጫ መረዳት ችለናል።