በቅርቡ ሥራ የሚጀምረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ሠራተኞች የኦን ላይን ስልጠና ተሰጠ

በቅርቡ ሥራ የሚጀምረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ሠራተኞች የኦን ላይን ስልጠና ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው ለሸገር ዳቦ ፋብሪካ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ አስታወቁ። ስልጠናው ለኢትዮጵያውያኑ በኦን ላይን እንደተሰጠም ሰምተናል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከካቢኔ አባላት ጋር በመሆን የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ያለበትን ደረጃ  ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ለዳቦ ፋብሪካው የሚያገለግሉ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች በኮሮና ቫይረስ ችግር ምክንያት በታሰበው ወቅት ወደ ሀገርለማስመጣት ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙም ፤ የማሽን ተከላው በሚያስገርም ፍጥነት እየተጠናቀቀ መሆኑን መመልከታቸውን ከንቲባ ታከለ ኡማ ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዐት ለምርት የሚሆን የግብዓት ዝግጅት የተጠናቀቀ  መሆኑንና የተወሰኑ ማሽኖች ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ፋብሪካው ወደሥራ እንደሚገባ ነው የተነገረው።

በዚህ መሠረት ሥራውን የሚያስጀምሩ፣ ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያዎች ወደሀገር ውስጥ መምጣት ባይችሉም “በኦን ላይን” ስልጠና በመስጠት ብቁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ማፍራት ተችሏል ብለዋል ከንቲባው በመግለጫቸው። “ሸገር ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ” ወደ ሥራ ሲገባ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ምርቱም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለ የማኅበረሰብ ክፍልን ባገናዘበ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑ ተነግሮለታል።

LEAVE A REPLY