በኢትዮጵያ 41 ሰዎች ሲያገግሙ ፣ አንድ የጅግጅጋ ነዋሪ ኮቪድ 19 ተገኝቶበታል

በኢትዮጵያ 41 ሰዎች ሲያገግሙ ፣ አንድ የጅግጅጋ ነዋሪ ኮቪድ 19 ተገኝቶበታል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ 957 ሰዎች ላይ  የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 123 ደርሷል:: ዛሬ በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ የ30 ዓመት የጅግጅጋ ነዋሪ ሲሆን ፤ ከፑንት ላንድ ተመልሶ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ መሆኑ ተሰምቷል።

ምርመራው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ የምርመራ ጣቢያዎች እየተካሄደ ሲሆን ፤ በኢትዮጵያ እስካሁን 13 ሺኅ645 ምርመራዎች ተደርገው 123ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። በቫይረሱ ከተያዙትም መካከል 41 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውና 12ቱ በትናንትናው ዕለት ያገገሙ መሆናቸው ተገልጿል።

LEAVE A REPLY