በዱባይ የሚኖሩ ከ4 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ምክንያት ከሥራ ተፈናቅለዋል

በዱባይ የሚኖሩ ከ4 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ምክንያት ከሥራ ተፈናቅለዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የሚኖሩ ከ4 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሥራቸው ተፈናቅለው ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ተሰማ።

በቀጣይም ከ20 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ችግር እንደሚገጥማቸው የገለፀው በዱባይ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጽ/ቤት  ቁጥሩም በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በዱባይ በአሁኑ ወቅት ሥራ አጥ መሆናቸው የተረጋገጠ፣ ከ4 ሺኅ በላይ ዜጐች በየቀኑ እርዳታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ እያቀረቡ ቢሆንም፤ ኮሚኒቲውና ቆንጽላ ጽ/ቤቱ በጋራ በሚያደርጉት ጥረት  ድጋፍ ማድረግ የቻሉት ግን በየቀኑ ለ250 ሰዎች ብቻ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከ7 ሺኅ ሰባት መቶ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 46 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ለችግር ከተዳረጉት ኢትዮጵያውያን መካከል የሚበዙት ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውንም ከተሰበሰቡ መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን ኮሚኒቲው ይፋ አድርጓል:: በችግሩ ውስጥ በአመዛኙ በሰው ቤት ሠራተኝነትና በዕለት ተዕለት ገቢ የሚያስገኙ አነስተኛ ሥራዎች ላይ የተሠማሩ ነበሩ ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY