ዛሬ ሌሊት በጂንካ በጣለ ዝናብ ከተማዋን የሚያገናኙ 2 ድልድዮች በጎርፍ ተወሰዱ

ዛሬ ሌሊት በጂንካ በጣለ ዝናብ ከተማዋን የሚያገናኙ 2 ድልድዮች በጎርፍ ተወሰዱ

Federal Democratic Republic of Ethiopia - vector map

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በደቡባዊቷ ጂንካ ከተማ ትናንት እኩለ ሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ በአካባቢው መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰማ፡፡

ከሌሊት ጀምሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ  ተከትሎ “ኔሪ” ተብሎ የሚጠራው ወንዝ በመሙላቱ በስፍራው ከፍተኛ ጎርፍ አስከትሏል።

በዚህም ምክንያት ከተማውን የሚያገናኙ ሁለት ድልድዮች  ሙሉ ለሙሉ በጎርፍ መወሰዳቸውን የዞኑ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል። ጎርፉመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በሰብል እና በእንስሳት ላይ  ተጨማሪ ጉዳት አድርሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትናንት በስቲያ ምሽትና ሌሊት ላይ በጣለ ከፍተኛ  ዝናብ ተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ በሚያጠቃት ድሬደዋ ከተማ አራት ሰዎች ሞተው በርካታ ንብረት መውደሙ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY