50 ሰዎች ከበኢትዮጵያ ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ተነገረ

50 ሰዎች ከበኢትዮጵያ ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ባለፉት 24  ሰዐታት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ከተደረገላቸው 943 ሰዎች መካከል አንድ ሰው ብቻ ቫይረሱ እንደተገኘበት ተነገረ።

በሌላ በኩል በበሽታው ተይዘው  ሕክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት ሰዎች መካካልም ዘጠኙ ከኮቪድ-19 በሽታ ማገገማቸው ተሰምቷል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዛሬ በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ዜጋ እና በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ መሆኑን መረዳት ተችሏል። እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ቁጥር 124 ሲሆን ከበሽታው ያገገሙት ሰዎች ደግሞ ሃምሳ ደርሰዋል ተብሏል።

በለይቶ ህክምና መስጫ ውስጥ የሚገኙት 69 መሆናቸውን የገለፀው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ ከባለፈው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ በአገሪቱ የምርመራ አገልግሎት የሚያገኙ ሰዎች አሃዝ በየዕለቱ ከዘጠኝ መቶ በላይ የደረሰ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ምርመራ የተደረገባቸው ቀናትም እንደነበሩም አስታውሷል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ለግንዛቤ ማስጨበጫ ይሆን ዘንድ ባሰራጨው መልእክት የኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው አካባቢዎች አይኖርም በሚል ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ በጥብቅ አሳስቧል። ቫይረሱ በየትኛውም የአየር ፀባይ ሊኖር እንደሚችል የተረጋገጠ በመሆኑም አመላክቷል።

LEAVE A REPLY