አዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ወር መጨረሻ በየቀኑ 80,000 ዳቦ ያገኛሉ ተብሏል 

አዲስ አበባ ነዋሪዎች በዚህ ወር መጨረሻ በየቀኑ 80,000 ዳቦ ያገኛሉ ተብሏል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቀን ከ80 000 በላይ ዳቦ ከማምረት ባሻገር  ከዚህ ቀደም የነበረውን ዋጋ በጥቂቱም ቢሆን የቀነሰ ያደርገዋል የተባለው “የሸገር ዳቦ ፋብሪካ “ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ተባለ፡፡

በአሁኑ ሰዐት አነስተኛ የኤሌክትሪክ መገጣጠም ሥራዎች እየተከናወኑለት የሚገኘው የዳቦ ፋብሪካው ሥራ ለመጀመር የሚያስችለው አስፈላጊው የስንዴ እህልም ጅቡቲ ወደብ መድረሱን ዛሬ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ግንባታውን በቶሎ ለማጠናቀቅ የኮሮና ቫይረስ መሰናክል ቢፈጥርም ከውጪ አገር ይመጡ የነበሩ የማሽን አካላት እዚሁ በአገር ውስጥ በመሥራት ሊደርስ ይችል የነበረውን መስተጓጎል ለማቃለል ተችሏል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ የተነሳ የሸገር ዳቦ ፋብሪካ አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር በያዝነው ሚያዝያ ወር መጨረሻ፣ አልያም በግንቦት መጨረሻ  ወደ ማምረት ሥራ በመግባት ዳቦውን ማከፋፈል እንደሚጀምር የፋብሪካው ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከአቶ ሲሳይ ደበበ ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY