ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ስታስገባ የነበረው ነዳጅ እንዲቀጥል በመንግሥት ደረጃ ድርድር ተጀመረ

ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ስታስገባ የነበረው ነዳጅ እንዲቀጥል በመንግሥት ደረጃ ድርድር ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ታስገባ የነበረው ነዳጅ እንዲቀጥል በመንግሥት ደረጃ ንግግር እየተደረገ ነው መባሉ ተሰማ።

ሱዳን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ድንበሯን መዝጋቷን ተከትሎ፣ በሀገሪቱ በኩል ይገባ የነበረው ነዳጅ አቅርቦት ተስተጓጉሏል።

በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ  የሆኑት አቶ ዓለማየሁ ፀጋዬ በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው 9 ሺ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን እንደሆነና  ይህ መጠን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከምታስገባው ነዳጅ 20 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን ተናግረዋል።

ቀሪው 80 በመቶው በጁቡቲ በኩል እንደሚገባ የጠቆሙት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ፤ በጁቡቲ በኩል ከሚገቡት መካከልም ቀላል ጥቁር ናፍታ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ከባድ ጥቁር ናፍታ ዋነኞቹ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመስጋት ድንበሯን የዘጋችው ሱዳን ከጥንቃቄ ጋር ነዳጅ የማስገባቱ ሥራ እንዲቀጥል ትፈቅድ ዘንድ የማግባባቱ ሥራ በሁለቱ መንግሥታት ደረጃ ቀጥሏል ተብሏል::

በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው ነዳጅ በአብዛኛው ለሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲሆን፤ የእነዚህ አካባቢዎችም አቅርቦት አሁን እየተሸፈነ ያለው በጁቡቲ በኩል በሚገባው ነዳጅ እንደሆነም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY