አረና ፣ ህወሓት ቀጣዮን ምርጫ በነሐሴ በትግራይ አካሂዳለሁ ማለቱን አልቀበልም አለ

አረና ፣ ህወሓት ቀጣዮን ምርጫ በነሐሴ በትግራይ አካሂዳለሁ ማለቱን አልቀበልም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በመቀሌ የመሸገው ህወሓት መራሹ መንግሥት፣ ቀጣዩን ምርጫ በተመለከተ ያወጣው መግለጫ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል አረና ፓርቲ ገለፀ።

በክልሉ ለዓመታት የህወሓት ተገዳዳሪ ሆኖ የዘለቀው “አረና ትግራይ ለአሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ” ፤ “ለሕገ መንግሥቱ ዘብ ቆሜያለሁ የሚለው የትግራይ ክልል (ህወሓት) ሕገ መንግሥቱን እየጣስ ነውና አንድ  ነገር ሊባል ይገባል” ሲል ለፌደራል መንግሥት ጥሪ አቅርቧል።

አረና ፣ ትህነግ በህዳር ወር ላይ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አውጥቶት የነበረውን ምርጫን የተመለከተ አቋም ዳግም እንደ አዲስ መለጠፉ ተገቢ ካለመሆኑ ባሻገር ሕገ መንግሥትን መጣስ ነው ሲል ይከስሳል፡፡

ይህ  የህወሓት ተግባር ሕገ ወጥ ነው ያለው አረና፤ “በትግራይ ክልል ለ7 ዓመታት ያህል ምንም አይነት ምርጫ አልተደረገም፤ ይህም ትህነግ ሳይመረጥ እየመራ ለመሆኑ ማሳያ ነው።  አሁንም የቀድሞውን መግለጫ መልሰው የለጠፉት የሕዝቡን ስሜት ለመለካት እንጂ ትክክለኛ አቋማቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው ” ብሏል።

የምርጫ ጉዳይ የሚመለከተው ምርጫ ቦርድን ነው በማለት የተናገሩት አቶ  አምዶም ገ/ሚካኤል አንድ ክልል ብቻውን ምርጫ እንዲያደርግ የሚያስችል መብት ደግሞ ህገ መንግስታዊ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፖርቲዎች በትህነግ የተቋቋሙ ሰለሆኑ እንደግፈዋለን ማለታቸው ብዙ አያስገርምም ይለሉ አምዶም ገ/ስላሴ፡፡

LEAVE A REPLY